🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የገጠርና ከተማ ሽግግርን በማሳለጥ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት እየጣለ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን የብራውን ፉድ የበቆሎ፣ ብቅልና አልሚ ምግብ ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ከፍተዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን እያሳደገ ነው።
ከለውጡ በፊት በደብረ ብርሃንና ሰሜን ሸዋ ዞን 18 ኢንዱስትሪዎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት በደብረ ብርሃን ከተማ መካከለኛና ዝቅተኛ ኢንዱስትሪዎች 105 እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን 87 መድረሳቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በየዓመቱም በአማካይ 24 መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት እየገቡ መሆኑን አንስተዋል።
በአማራ ክልል የተቀጣጠለው የኢንዱስትሪ አብዮት የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን እያሳደገ ነው ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ምርታማነት ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር የሉዓላዊነትና ራስን የመቻል የኢትዮጵያ ብልጽግና ማብሰሪያ መሆኑንም ተናግረዋል።
መንግስት የዘርፉን ማንሰራራት የሚያጎሉ የፖሊሲ፣ የአደረጃጀት፣ የግብዓት፣ የመሠረተ ልማት፣ የፋይናንስና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎች ማድረጉንም አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ አምራች ኢንዱስትሪ የገጠርና ከተማ ሽግግርን በማሳለጥ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት እየጣለ ነው።
የብራውን ፉድ ፋብሪካም የሚጠቀመው የአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ኩንታል የበቆሎ ግብዓት የገጠርና ከተማ ሽግግርን ለማሳለጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ፋብሪካው በየዓመቱ ከ36 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች አስተማማኝ የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ከፍተኛ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።
በዚህም የአርሶ አደሩን ገቢና ኑሮ በማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማሳለጥ እንደሚረዳ አብራርተዋል።
የፋብሪካው ምርትም የቢራ አምራቾችን የብቅል አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል ያሉት ሚኒስትሩ ፤ በምርት አቅርቦት ቅብብሎሽ ውስጥ ያሉ ተዋናዮች እና የኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026