🔇Unmute
ድሬዳዋ፤ ግንቦት 26/2018(ኢዜአ)፦ በምርጫው ሂደት ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያሳየነውን ጠንካራ ተሳትፎ በልማትም እናስቀጥላለን ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 24 በተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የማለዳው ቅዝቃዜና የምሽቱ ጨለማ ሳይበግራቸው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
የምርጫውን ሂደትና የነበረውን ተሳትፎ በማስመልከት የኢዜአ ሪፖርተር በድሬዳዋ ከተማ ተዘዋውሮ ነዋሪዎችን አነጋግሯል።
ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት በምርጫው ሂደት ለዴሞክራሲ እውን መሆን ያበረከቱትን አስተዋፅኦ፣ በከተማዋ የልማትና የዕድገት ጉዞ ላይ ለማስቀጠል እንደሚተጉ ገልጸዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ምንዳ ሰለሞን እና ወይዘሮ ማህሌት ታደለ፤ በድምፅ አሰጣጡ የነበራቸው ተሳትፎ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የምትመች ሀገር የመገንባት ሃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም በምርጫው ሂደት ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያሳየነውን ጠንካራ ተሳትፎ በልማትም እናስቀጥላለን ነው ያሉት።
አቶ አለማየሁ በቀለ፣ ወይዘሮ ከድራ ኡስማን እና አቶ ግርማ በዛዬ በበኩላቸው፤ በታሪካዊው ምርጫ መሳተፍና ድምፅ መስጠት ሀገራዊ ሃላፊነት መሆኑን አንስተው፤ የምርጫ ሂደቱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ በጥሩ መሰረት ላይ የሚያኖር መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም በምርጫው ያሳየነውን ጠንካራ ተሳትፎ በቀጣይ የሀገር ልማትና የሰላም ግንባታ ሂደት ላይ ለማስቀጠል ዝግጁ ነን ብለዋል።
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...
Jul 13, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...
Jul 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢ...
Jul 7, 2026