የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ ኢኮኖሚያዊ ሉዐላዊነቷን እንድታስከብር መሰረት ይጥላል

Jun 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና፤ ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ የኢኮኖሚ ሉዐላዊነቷን ለማስከበር መሰረት ይጥላል ሲሉ የዋቸሞ እና የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ምሁራኑ ተናግረዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ የዋቸሞ እና የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ሞያዊ ማብራሪያ ጠይቋል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዳንኤል ሀንዲኖ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከባህር በር ተነጥላ እንድትኖር የተደረገበት ኢፍትሃዊ መንገድ ቅቡልነት የለውም።

በዚህም ላለፉት ዓመታት ለተለያዩ ችግሮች ተዳርጋ ቆይታለች ያሉት ዳንኤል (ዶ/ር)፣ ከዚህ ችግር ለመውጣት መንግስት በዲፕሎማሲያዊ መንገድና በሰጥቶ መቀበል መርህ የጀመረው ጥረት እንዲሳካ የሁሉም አስተዋጾ መጠናከር አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ የኢኮኖሚ ሉዐላዊነቷን ለማስከበር መሰረት እንደሚጥል ገልጸው፣ ጥያቄው ታሪካዊ እና ህጋዊ መሰረት ያለው ከመሆኑ ባለፈ ለሀገር እድገት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋል ብለዋል።

መንግስት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ያላትን ጽኑ ፍላጎት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስገነዘበበት ሂደት የሚደገፍና የሚበረታታ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ዜጎች አስተዋጿቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

ሌላው በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አባስ ሉቅማኔ በበኩላቸው እንዳሉት፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በፈጣን እድገት ላይ ለሚገኙ ሀገራት የባህር በር ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም።

በአሁኑ ወቅት ከ130 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ቁጥር ያላትን ኢትዮጵያ የባህር በር ማሳጣት እድገቷ በተፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ ይገድባል ሲሉም ጠቁመዋል።

ለዘመናት የባህር በር ባለቤት የነበረች ሀገር ላለፉት በርካታ ዓመታት ከባህር በር እንድትነጠል መደረጉ ከፍተኛ ገንዘብ ለወደብ ኪራይ እንድታወጣ ከማድረጉ ባለፈ በወጭና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ችግር ለመውጣት ዓለም አቀፍ ህግንና ታሪካዊ ባለቤትነትን መሰረት በማድረግ የባህር በር ባለቤትነቷን ዳግም ለማረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት በሞያቸው ለመደገፍ ዝግጁነታቸውንም አረጋግጠዋል።

የባህር በር ባለቤትነት ፈጣን ምላሽ ማግኘትም ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ለቀጣናው ሀገራት የእርስ በርስ ትሰስርና ሰላም መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት ከምስል ጋር!

  የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...

Jun 4, 2026

በዲጂታል ክህሎት ራሳችንን እያበቃን ነው - ተማሪዎች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...

Jun 1, 2026

በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል

አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...

May 25, 2026

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው

ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...

May 15, 2026