የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የታክስ አሰራርን በማዘመን ፍትሐዊነትና የሕግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ እገዛ ያደርጋል

Jun 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018 (ኢዜአ)፡- የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የታክስ አሰራርን በማዘመን ፍትሐዊነትና የሕግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የአስረጂ መድረክ ተካሂዷል።


የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቃዱ ሆረታ በዚህ ወቅት፤ የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ከኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ዘመናዊ የታክስ አሰራር ለመፍጠር ያስቻላል ብለዋል።

በታክስ ከፋዩ ማህበረሰቡ የሚነሱ መሰረታዊ የፍትሐዊና የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችንም መፍትሔ ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የመንግሥትን ገቢ የመሰብሰብ አቅም በማጎልበት ተጠያቂነትን ከግልጸኝነት ያጣመረ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ አባላትና የሕግ ማዕከል ባለሙያዎችም፤ በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የታክስ ስሌት፣ የይርጋ ጊዜ ገደብ፣ የታክስ ከፋይ መስተንግዶና ተያያዥ ጉዳዮችን በማስመልከት ጥያቄ አንስተዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ዋሲሁን አባተ፤ በረቂቅ አዋጁ የይርጋ ጊዜው አስር ዓመት ሆኖ መቀመጡ በታክስ ከፋዩ ላይ የሚኖረውን ጫና መቀነስ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፈ ተወዳጅ መሐመድ፤ የታክስ ደረሰኝ አለመስጠት ተመሳሳይ የገንዘብ ቅጣት መጣሉ ሆን ተብሎ የሚፈጸምን የታክስ ማጭበርበር በማስቀረትና ደረሰኝ መቁረጥን ባህል ያደርጋል ብለዋል።

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ አማካሪ ያሬድ ፍቃደ በበኩላቸው፤ የገለልተኛ አስማሚ ስርዓት ገለልተኛ ሆኖ የሚቋቋም በመሆኑ ግብር ከፋዩ የሚገጥመውን ችግር መፍቻ ተጨማሪ አማራጭ ነው ብለዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጀ፤ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ልክ ገቢን ለመሰብሰብና የታክስ አስተዳደርን ለማዘመን እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በአስረጂ መድረኩ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ይበልጥ ማጥራት የሚያስችል ማብራሪያ መሰጠቱን ጠቁመው የተደረጉት ማሻሻያዎች ፍትሐዊነትንና የሕግ ተገዢነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026