የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል

Jun 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሰኔ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ለመኸር ሰብል ልማት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሽራ ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በክልሉ በ2018/2019 የምርት ዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ ግብዓትን ለአርሶ አደሩ በወቅቱ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ ነው።

ለምርት ዘመኑ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን ከ4 ሚሊዮን 822 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያን ወደ ክልሉ በማጓጓዝ ለአርሶ አደሩ የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁንም ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው እንደተሰራጨ የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ የማዳበሪያ አቅርቦቱ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በምርት ዘመኑ 220 ሺህ ኩንታል የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘር ለማቅረብ በታቀደው መሰረት እስካሁን 137 ሺህ 675 ኩንታል ለአርሶ አደሩ ደርሷል ብለዋል።

የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦቱ በወቅቱ መካሄዱ አርሶ አደሩ ምርታማነቱን በማሳደግ የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባሻገር ለገበያ የሚተርፍ ምርት በአይነት፣ በብዛትና በጥራት እንዲያመርት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክተዋል።

"በመኸር ምርቱ ምንም አይነት የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም እየተሰራ ነው" ያሉት ወይዘሮ ሙሽራ፣ አስፈላጊውን ግብአት ለማቅረብ በየደረጃው በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ ማይነት ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጋቴ ጎሸ እንደገለጹት ለዘር የሚያስፈልጋቸውን አምስት ኩንታል ማዳበሪያ ቀድሞ ማግኘታቸው የዘር ሥራቸውን ያለምንም ችግር ለማከናወን አግዟቸዋል።

በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ እንጉቲ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ስሜነህ አበረ በበኩላቸው፤ የዘንድሮው የግብርና ግብዓት አቅርቦት ወቅቱን ጠብቆ መከናወኑን ተናግረዋል።

ይህም የዘር ሥራቸውን ፈጥነው በማከናወን የተሻለ ምርት እንዲያገኙ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው ያስታወቁት።

በአማራ ክልል በመኸር ወቅት 5 ነጥ 6 ሚሊየን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በማልማት ከ205 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደስራ መገባቱን ከቢሮው የተገ መረጃ ያስረዳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026