🔇Unmute
ደብረ ብርሃን፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ)፡- በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ ከተሞችን የኮሪደርና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰራው ስራ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ማሳደጉ ተመላከተ።
በዞኑ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የመሰረተ ልማት ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ አንተነህ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ ከተሞች እየተገነባ ያለው የኮሪደር ልማት የኢንዱስትሪ፣ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲፋጠን አድርጓል።
በዚህም በዞኑ የሚገኘውን ማዕድንና ሌሎች ጸጋዎች በማልማት ለአገር እድገትና ለህዝብ ዘላቂ ጥቅም ለማዋል ማስቻሉን ገልጸዋል።
ባለፈው ዓመት በሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በማስቀጠል ዘንድሮ በዓለም ከተማ፣ በአጣዬ፣ በአረርቲና በለሚ ከተሞች የማስፋት ስራ መሰራቱን አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማቱ የእግረኛ፣ የተሽከርካሪና የሳይክል መንገድን፣ የመብራት፣ የውሃና የቴሌኮም መስመር ዝርጋታንና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን አካቶ እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ለከተሞቹ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትና ገጽታ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በከተሞቹ ከ81 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የኮብል ስቶን፣ የጠጠር መንገድ ግንባታና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችን በመገንባት ማጠናቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026