የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ለከተማዋ ንግድና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው

Jul 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ፤ ሀምሌ 9/2018 (ኢዜአ)፡- የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ስራ መጀመር ለከተማዋ ንግድና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደብረ ማርቆስ ንጉስ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን ከቀናት በፊት መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።

የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቱ ተመርቆ ስራ መጀመርን ተከትሎ ኢዜአ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ተመስገን ተድላ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በቆይታቸውም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቱ ስራ መጀመር በተለይም ኢንቨስትመንትን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ጊዜያቸውን በመቆጠብ እና በልማቱ ስኬታማ ከመሆን ባሻገረ ለፈጣንና ቀልጣፋ የገበያ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ስራ መጀመር ለከተማዋ ንግድና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስና አካባቢው ለኢንቨስትመንት ሰፊ እድሎች መኖራቸውን ያነሱት ኃላፊው ባለሃብቶች ይህንን እድል እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።


በከተማዋ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ታመነች ታደለ፣ አቶ ነብዩ ብርሃኑ እና ወጣት ተጎዳን ፈጠነ፤ የረጅም ዓመታት ጥያቄያችን ተመልሶ ኤርፖርቱ ስራ በመጀመሩ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ስራ መጀመር የኢንቨስትመንትና ንግድን በማነቃቃት አዳዲስ የስራ እድል እንዲከፈት የሚያደርግ ነው ብለዋል።


የኤርፖርቱ መገንባት ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ባለፈ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት መሳለጥም ትልቅ አቅም መሆኑን አንስተዋል።

የደብረ ማርቆስ ኤርፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ ጥያቄ የ30 ዓመታት የአካባቢው ህብረተሰብ ጥያቄ የነበረ ሲሆን በለውጡ መንግስት በጥቂት ዓመታት ውስጥ ምላሽ ያገኘ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 14, 2026

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...

Jul 10, 2026

የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር ያስችላል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢ...

Jul 8, 2026

የቦንጋ ከተማን እድገትና ልማት በማፋጠን ለነዋሪቿ ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው 

ቦንጋ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ):- የቦንጋ ከተማን ዕድገትና ልማት በማፋጠን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የካፋ ዞን አስ...

Jun 29, 2026