🔇Unmute
ጎንደር፤ ሐምሌ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በከተሞች መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመገንባት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላት የተቀናጀ ጥረት የሚደረግ መሆኑን የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ገለጸ።
በክልሉ በተለይም በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የተቀናጀ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በዚህ የልማት ጥረት ውስጥ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በጡብ ማምረት ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ስልጠና በጎንደር ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ አማካሪ አቶ ሽቤ ክንዴ፤ ኮሌጆቹ ቴክኖሎጅን የመቅዳት፣ የማላመድና የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም የቤት ግንባታ ፕሮጀክት እቅዱ እንዲሳካ መስራት አለባቸው ብለዋል።
በዘመናዊ መንገድ ጡብ በማምረት በከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ውብና ማራኪ ቤቶችን መገንባት አለብን ያሉት አቶ ሽቤ፤ ለዜህም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ከፍተኛ ሚና እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የዚህ ስልጠና ዋነኛ ዓላማም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ለእቅዱ መሳካት የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም ለልማት ፕሮጀክቱ ስኬት የበኩላቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)፤ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችን ለመገንባት እቅድ መያዙን መግለፃቸው ይታወቃል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026