የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ታዋቂው ሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

Aug 5, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ታዋቂው የሲኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ባለፈ የቀጣናው ሀገራትን የኢነርጂ ተጠቃሚ ያደረገ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን በዘገባው አስቃኝቷል።


ግድቡ በሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ብርሃን ያደረሰ መሆኑንም አመላክቷል።


በሲኤንኤን ዘጋቢ የሆነችው ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ባሰናዳችው ዘገባ÷ ወደ ጉባ በማቅናት የግድቡን እውነታ አስቃኝታለች።


በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ የምህንድስና ባለሙያዎች እና የግንባታ ባለሙያዎች ሸለቋማ የሆነውን አካባቢ ወደ አፍሪካ ግዙፍ ግድብ መቀየራቸውን ገልጻለች። ግድቡ የምህንድስና ልህቀት የታየበት ነውም ብላለች።


ከ14 ዓመታት የግንባታ ቆይታ በኋላ ህዳሴ ግድብ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር መስከረም 2025 መመረቁን ገልጻለች።


ግድቡ በኢትዮጵያውያን ድጋፍ፣ የመንግስት ፋይናንስ፣ ቦንዶች እና የተለያዩ የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አማራጮች በኢትዮጵያዊያን አቅም መገንባቱን ተናግራለች።


ይህ ግዙፍ ግድብ ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያውን ብርሃን የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራትም የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እንዲደርስ የሚያደርግ ነው።


በዚህም ግድቡ ከኢትዮጵያ ባለፈ የቀጣናዊ ኃይል ትስስር ማእከል እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግራለች።


ሲኤን ኤን በዘገባው ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን በማቅረብ ኢትዮጵያ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት በማይጎዳ መልኩ ግድቡን እየተጠቀመች መሆኑን አመላክቷል።


ግብፅ በግድቡ ምክንያት የሚደርሳት ውሃ ቀንሷል በሚል የምታቀርበው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑንም ኢንጂነር ክፍሌ አስረድተዋል፡፡


አሁን ላይ በሕዳሴ ግድቡ የሚገኙ 13 ተርባይኖች በሚያመነጩት ሀይል 6 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ ሀይል ተደራሽ ማድረግ መቻሉን፣ በቀጣይ ደግሞ ለሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሀይል ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል፡፡


በተጨማሪም በሕዳሴ ግድቡ በተፈጠረው ንጋት ኃይቅ ላይ የተፈጠሩት ደሴቶች ለቱሪስት መስህብነት ትልቅ አቅም መሆናቸውን በማንሳት ፤ በቀጣይም ለቱሪስት መዳረሻነት የሚያገለግሉ መሰረተ ልማቶች እንደሚገነቡ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 13, 2026

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...

Jul 9, 2026

የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር ያስችላል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢ...

Jul 7, 2026