🔇Unmute
ሐረማያ፤ ሐምሌ 30/2018(ኢዜአ) ፦ በመደመር መንግስት እሳቤ የተከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት የዜጎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻላቸውን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
በመደመር መንግሥት እሳቤ የሕዝብን ተሳትፎ፣ የሀገር በቀል እውቀትንና ውስጣዊ አቅምን በማስተባበር እንደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብና የአረንጓዴ አሻራ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በስኬት ማከናወን ተችሏል።

እነዚህ የጋራ ጥረቶችም የአካባቢ ጥበቃን ከማረጋገጥ ባሻገር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት፣ የምግብ ዋስትና እና የሥራ ዕድል ፈጠራን በማሳለጥ ለሀገራዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም የሚታይ ሀቅ ነው።
ምሁራኑ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በተለይ በመደመር መንግስት እሳቤ በሕዝብ ተሳትፎ የተከናወኑ ተግባራት የጋራ ጥረት ሀገራዊ ለውጥን ለማምጣት ማረጋገጫ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በፖለቲካው ዘርፍም አሰባሳቢ ትርክትን ለመገንባት የተጀመሩ ጥረቶችና በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ መሥራት መቻሉም ውጤት እየታየበት መሆኑን አንስተዋል።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብትና የአካባቢ ምሕንድስና መምህርና ተመራማሪ ኤሊያስ ጀማል (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በመደመር መንግሥት እሳቤ ለሀገር ልማት በተናጠል የሚደረግን ሩጫ ገታ በማድረግ የጋራ እሴትን በመጠቀም አቅም ለመፍጠር መሠራቱን አስረድተዋል።
እሳቤውን መሰረት በማድረግም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ዜጎች በነቃ ተሳትፎ እንዲመሩ በማድረግ ተጨባጭ ልማት ለማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል።

በህብረተሰብ የልማት ተሳትፎ ረገድ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብንና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ለአብነት አንስተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ የማንንም ድጋፍ ሳትሻ በዜጎቿ ትብብር ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በማቀናጀት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ባለፈ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እየተጋች መሆኑን ለዓለም ያሳየችበት ነው ብለዋል።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም መምህርና ተመራማሪ ዳኒ ረሺድ በበኩላቸው በመደመር መንግሥት እሳቤ ዜጎች የነቃ ተሳትፎ የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የአካባቢ ጥበቃ ባህል እንዲያድግ ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።
በተለይም በበጎ ፈቃድ ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ ተግባራት የጠፉ ሐይቆች እንዲመለሱና የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሃ ሀብት እንዲጨምር ማገዛቸውን አስረድተዋል።
ለዚሁ ማሳያ ለዓመታት ጠፍቶ የነበረውን የሐረማያ ሐይቅ ከመመለስ ባለፈ የመስኖ ልማት እንዲጎለብት ማድረጉን ተናግረዋል።
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችም የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ማገዛቸውንም አክለዋል።
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...
Jul 13, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...
Jul 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢ...
Jul 7, 2026