🔇Unmute
ገንደ ውኃ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከመደበኛና ከከተማ አገልግሎት ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንየዞኑ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ደብሬ ብርሃኑ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ የዞኑ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት ለማዋል ጥረት ተደርጓል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከመደበኛና ከከተማ አገልግሎት ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንም ገልጸዋል።
በዚሁ ወቅት የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ457 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
ገቢውን መሰብሰብ የተቻለውም ከመደበኛና ከከተማ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመው፣ ለስኬቱም የዘርፉ ባለሙያዎችና በየደረጃው ያለው አመራር በቅንጅት መስራታቸውን አንስተዋል።
በአዲሱ በጀት ዓመትም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግብር አከፋፈል ሥርዓትን በመዘርጋት ነጋዴው ጊዜውንና ጉልበቱን በመቆጠብ በተለያዩ አማራጮች እንዲከፍል ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው ፤ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ለአካባቢው መሠረተ ልማት ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በገንዳውኃ ከተማ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩት አቶ አበበ ከበደ እና ወይዘሮ አስቴር ዓለሙ እንደሚሉት፤ ግብር መክፈል ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በመረዳት በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ተወጥተዋል።
ተቋሙ በፈጠረው ግንዛቤ ግብርን በቀላሉና በወቅቱ እንዲከፍሉ ያደረገ ሲሆን፣ የተሰበሰበው ገቢም በከተማዋ ለመሠረተ ልማት ግንባታ በመዋል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እየተቻለ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ የመተማ ዮሐንስና የምድረ ገነት ከተማ አስተዳደሮች፣ የመተማና የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳዎች በበጀት ዓመቱ የተሻለ ገቢ የሰበሰቡ መሆናቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...
Jul 13, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...
Jul 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢ...
Jul 7, 2026