
በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ የሚታይ ምንነቱ ያልታወቀ ተቀጣጣይ ነገር መመልከታቸውን በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በተለያዩ አማራጮች መረጃውን አጋርተዋል።
ተቀጣጣይ ነገሩን የሚያሳዩ መረጃዎች በፎቶ እና በተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለመመልከት ተችሏል።
ጉዳዩ የብዙዎችንም ቀልብ የሳበ ጉዳይ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ስፔን ሳይንስ ሶሳይቲ ትናንት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸውን አስመልክቶ ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል።
ሶሳይቲው በደረሰው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ባደረገው ምልክታ የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ይመስላሉ ሲል አመልክቷል።
ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ነው ያስታወቀው።
የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት እንዲቻል ሁኔታውን በቅርበት እያጣራ እንደሚገኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚያቀርብ ገልጿል።
ይህ የማጣራት ሥራ እንኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ ሶሳይቲው አሳስቧል።
በተጨማሪም ሶሳይቲው የቁስ አካላቱን አስመልክቶ እያደረገ ላለው ማጣራት የአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረጿቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች በመላክ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026