የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

Feb 24, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጋትሉዋክ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት በተያዘው በጀት ዓመት የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በክልሉ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት ህብረተሰቡን በማህበራዊና በኢኮኖሚ የልማት መስኮች ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ የተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ቢኖሩም በተለያዩ ምክንያቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ሳይበቁ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተያዘው በጀት ዓመት እነዚህን ያደሩ ፕሮጀክቶች አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የክልሉ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የውሃ߹ የመስኖ߹ የትምህርት߹ የቢሮ ግንባታና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ በጥናት ላይ ተመስርቶ ወደ ስራ መገባቱን አብራርተዋል፡፡

በጋምቤላ ከተማ ለቢሮ አገልግሎት እንዲውሉ ታስበው እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎችን አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግም ያልተቆጠበ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የተጀመሩ ነባር ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ ከኮሪደር ልማት በስተቀር ሌሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይጀመሩም ተናግረዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በክልሉ የኮሪደር ልማት የመጀመሪያው ምዕራፍ በጋምቤላ ከተማ በይፋ መጀመሩን ጠቅሰው፤ በዞኖችና በወረዳዎችም ስራውን ለማስጀመር የግንዛቤ ማስጨበጫ መከናወኑንና በቅርቡም ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በክልሉ በመከናወን ላይ ያሉ ነባር ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ሲበቁ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያጠናክሩ እንደሚሆኑም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025