የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

Feb 28, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የክልሉ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡


በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ከ102 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአሞገራ- አስጠር የ21 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ እና ድልድዮች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ኑሪዬ (ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማስፋፋት እየተሰራ ነው፡፡


በክልሉ መንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን የማከናወን ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው ተናግረዋል።


ለአገልግሎት የሚበቁ ፕሮጀክቶች ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡


የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው፥ በዞኑ በበጀት ዓመቱ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በ2016 በጀት ዓመት 243 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ ማከናወን ተችሏል ብለዋል።


በዚህ በጀት ዓመት ደግሞ በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ210 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ 300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ቀበሌን ከቀበሌ እንዲሁም ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ የጠጠር መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።


በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ትዛዙ ቢረዳ እንደገለፁት፥ በክልሉ ግንባታቸው የዘገየና አዲስ የተጀመሩ 830 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው እየተከናወነ ይገኛል፡፡


እነዚህን መንገዶች ደረጃ በደረጃ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።


ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የአሞገራ-አስጠር የ21 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ እና ሌሎች አራት ድልድዮች የአካበቢው ማህበረሰብ ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ በማውጣት ተገቢ ዋጋ እንዲያገኙ የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።


የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹን ለማጠናቀቅ ከ102 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ማህበረሰቡ በጥንቃቄ ሊጠቀምባቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡


ከመንገዱ ተጠቃሚዎች መካከል አርሶ አደር ሚስባህ መሀመድ እና አቶ መብራቴ ተክሌ በአካባቢው በመንገድ እጦት ሳቢያ ለከፍተኛ እንግልት ሲዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል።


የሚያመርቱት ምርት ሳይባክን ወደ ገበያ ለማቅረብ እና የአፈር ማዳበሪያ እስከ ማሳቸው ለማስገባት መንገዱ ሚናው ጉልህ ነው ብለዋል።


ሌላኛዋ የዞኑ ነዋሪ ወይዘሮ አለም አብድራህማን መንገድ እና ድልድይ ባለመኖሩ ለተለያዩ ችግሮች ሲጋለጡ መቆየታቸውን አንስተዋል።


የመንገድ እና ድልድዮቹ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት በመብቃታቸው መደሰታቸውን ገልፀው፥ ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ በጥንቃቄ ለመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...

Jul 27, 2026

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...

Jul 21, 2026

ከአፍሪካ ትልሞች ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...

Jun 27, 2026

በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት አውጥተዋል

ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...

Jun 26, 2026