አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2017(ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) መርቀው መክፈታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ይኽ ተግባር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በማዘመን ረገድ ዐቢይ ርምጃ መሆኑንም ገልጿል።
ESX ለዘርፉ ግልፅነትን የተላበሰ የገበያ ስፍራ ይፈጥራል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጥላ ሥርም በኢንቨስትመንት ለሚመራ እድገት በር ይከፍታል ነው ያለው።
በመንግሥትም በግልም ዘርፎች የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት የቁጠባ እንቅስቃሴን ማሳደግን ብሎም ኢንቨስተሮችን መጠበቅን ታላሚ አድርጎ ተነስቷል ሲልም ገልጿል።
ESX በሶስት የገበያ ክፍሎች ላይ ይሰራል ያለው ጽህፈት ቤቱ እነዚህም ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግሥት እና ሌሎች ተቋማት የሚያገለግሉ የይዞታ ገበያ፣ የቋሚ ገቢ ገበያ እና የገንዘብ ገበያ ናቸው ብሏል።
የሙከራ የገንዘብ ገበያው ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ እንቅስቃሴ ተካሂዶበታል ሲልም አስታውቋል።
ይኽም ገበያው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር ብሎም ለዘላቂ ልማት የካፒታል አቅም ለማሰባሰብ ያለውን አቅም አሳይቷል ነው ያለው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025