
ባሕር ዳር፤ ጥር 05/2017 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ለገበያ አለመረጋጋት በሚዳርጉ ሕገ ወጥ ግብይት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ።
ቢሮው የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት እንዲቻል ከተለያዩ የሀብት ምንጭች በማሰባሰብ 960 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል።
የቢሮው ሃላፊ ኢብራሒም ሙሐመድ(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የክልሉን ሰላም ከማጽናት በተጓዳኝ የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
በተለይም ለገበያ አለመረጋጋት በሚዳርጉ ህገ ወጥ ግብይት ላይ ተሰማርተው በተገኙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አንስተዋል።
በግማሽ ዓመቱ በሕገ-ወጥ ግብይት የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ከ55 ሺህ 454 በላይ ነጋዴዎች በሕገ-ወጥ ግብይት ሲፈጽሙ መያዙን ገልጸዋል።
በዚህም እንደ ጥፋታቸው ከማስጠቀቂያ እሰከ ማገድ እንዲሁም በሕግ ተጠያቂ እስከ ማድረግ የደረሱ እርምጃዎች ተወስደዋል ነው ያሉት።
ነጋዴዎቹ ያለንግድ ፈቃድ ግብይት በመፈጸም፣ በምርት ጥራት ጉድለት፣ ትክክለኛ ያልሆነ የመለኪያ መሳሪያ በመጠቀም፣ በተጋነነ ዋጋ እና ያለደረሰኝ በመሸጥ ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው ብለዋል።
ከ250 ሺህ ሊትር ነዳጅና አምስት ሺህ 573 ኩንታል የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶች መያዙንም እንዲሁ።
ከሕገ ወጥ ግብይት ቁጥጥር ባሻገር ከተለያዩ የሀብት ምንጮች ሀብት የማሰባሰብና የብድር አማራጭ በማቅረብ፣ የሕብረት ስራ ማህበራትን የካፒታል አቅም ችግር በመፍታትም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ለአብነትም 960 ሚሊዮን ብር ከተለያዩ የሀብት ምንጮች በማመቻቸት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለተጠቃሚው በማቅረብ ለገበያ መረጋጋትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡ ሕገ-ወጥ ግብይት ሲፈጸም ሲያስተውል ለሚመለከተው አካል ፈጣን ጥቆማ በመስጠት ሚናውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026