
አክሱም፣ጥር 6/2017 (ኢዜአ)፦በአክሱም ከተማ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሐዱሽ ገብረመድህን ለኢዜአ እንደገለጹት፤በበጀት ዓመቱ የአክሱም ተለዋጭ መናኸሪያን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች እየተካሄዱ ነው።
የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ ለከተማዋ ነዋሪዎች የተሻለ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ብለዋል።
ከሚገነቡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መካከል የ1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣የመንገድ ዳር መብራትና የ5 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።
በተጨማሪም በክረምት ወራት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች 1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።
የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹም ለ1 ሺህ 400 ስራ አጥ ወገኖች የስራ እድል ተፈጥሯል።
የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል የንግስተ ሳባ ቀበሌ ነዋሪው ወጣት አቤሰሎም ዜናዊ ከሥራው በሚያገኘው ገቢ የመነሻ ካፒታል ተጠቅሞ የግሉን ስራ ለመጀመር ሀሳብ እንዳለው ገልጿል።
የሐወልቲ ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ሙሉ ካህሳይ በበኩሏ በተፈጠረላት የስራ ዕድል በምታገኘው ገቢ ወደ ዘላቂ ሥራ ለመሸጋገር እቅድ እንዳላት ተናግራለች።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026