የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ተቋማቱ በችግር ፈቺ የፈጠራ ምርቶች ምን ያህል ውጤታማ ሆነዋል?

Jan 18, 2025

IDOPRESS

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ግብ ችግር ፈቺ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን ዕውን ማድረግ ነው።

ዘርፉ የኢንዱስትሪላይዜሽን ጉዞ መስፈንጠሪያ ነው። በተለይም የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀሩ ሀገራዊ ተኪ ምርቶችን በማምረት።

በዚህም ተቋማቱ አንድም በምርምርና ፈጠራ ስራዎችን ውጤታማ መሆን፣ አንድም በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ብቁና በቂ የሰው ኃይል የማፍራት ግብ ሰንቀው ይሰራሉ።

ተቋማቱ የፈጠራ ውጤቶችን በተግባር ከማዋል በዘለለ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ረገድም አይተኬ ሚና ይጫወታሉ።

በኢትዮጵያም ይህ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶት በርካታ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ተቋቁመው ወደስራ ገብተዋል።

ለመሆኑ ተቋማቱ በችግር ፈቺ የፈጠራ ምርቶች ምን ያህል ውጤታማ ሆነዋል የሚለውን ኢዜአ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ለአብነት ቃኝቷል።

የኮሌጁ መምህር ወርቁ ፈንታሁን እና ተማሪ ዳግም ጋርጦ ኮሌጁ እና የኮሌጁ ሰልጣኞች ቁልፍ ግባቸው ችግር ፈቺነት ነው ብለው ያምናሉ።

መምህሩና ደቀ መዝሙሩም በቅርብ የተመለከቱትን ችግር የሚፈታ የፈጠራ ስራ ለማውጣት ወሰነው ወደስራ ገብተዋል።

መምህር ወርቁ ከሩቅ ሳይሆን ከቅርብ ችግር ተነስተው የእንስሳት መኖ ማቀነባበርያ ማሽን መስራት ችለዋል።

ይሄውም በሚያስተምሩበት የጀኔራል ዊንጌት ኮሌጅ የሚካሄደውን የከብት እርባታና ማድለብ ስራ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው የመኖ እጥረት የመኖ ማቀነባበሪያ ለማምረት ምክንያት ሆኗቸዋል።

ፈጠራቸውም የኮሌጁን ችግር አቃሏል። ይኼውም ኮሌጁ ለእንስሳት መኖ ግዢ የሚያወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ ማስቀረታቸው ነው።

መምህር ወርቁ እንደሚሉት ማሽኑ ከውጭ ቢገባ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚጠይቅ ሲሆን እርሳቸው ግን በ400 ሺህ ብር ብቻ ሀገር ውስጥ መተካት ችለዋል።

ማሽናቸው በሰዓት 4 ኩንታል፤ በቀን ደግሞ 15 ኩንታል መኖ ያቀነባበራል። ከአዋጭነት አኳያም በወር እስከ 100 ሺህ ብር ትርፍ ያስገኛል ይላሉ።

የመኖ ማቀነባበርያ ማሽኑን በብዛት አምርቶ በአዲስ አበባ በከተማ ግብርና ለተሰማሩ አካላት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ይገልጻሉ።

የኮሌጁ ተማሪ ዳግም ጋርጦ ደግሞ አካል ጉዳተኞችን፣ አቅመ ደካሞችንና ህፃናትን መመገብ የሚያስችል ሮቦት ነው የሰራው።

ሮቦቱ ለአንድ ሰው በቀን የሚመገበውን ምግብ እና የሚጠጣውን ውሃ በልኬት በተሰጠው መጠን ልክ ድጋፍ ለሚሹ ህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችላል።

ለህብረተሰቡ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ መስራት ለሀገር ያለውን ወሳኝ ፋይዳ የሚያነሳው ዳግም፤ ለዚህ ደግሞ ለዘርፉ ምቹ ምህዳር ሊፈጠር እንደሚገባ ያነሳል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂና የኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ መሀመድ ልጋኔ እንደሚሉት በከተማዋ በሚገኙ 15 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ብቁና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ተተኩሯል።

ማሰልጠኛ ተቋማት ችግር ፈቺ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን በማውጣት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ እያደረጉ እንደሆነም ይገልጻሉ።

እስካሁንም ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ጥሬ ግብዓቶች በመጠቀም ተኪ ምርቶችን በማምረት ምሳሌ የሆኑ ኮሌጆች እንዳሉ የጀኔራል ዊንጌትን ለአብነት ይጠቅሳሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025