
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፥ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ኢትዮጵያ እየተገበረች የምትገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች፣ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2025 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ጉባዔ አስመልክቶ እያደረገች ያለው ዝግጅት ሌሎች የውይይት አጀንዳዎች ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቡድን (UNCT) እና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያላቸውን አጋርነት በማጠናከር የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ መደገፍ የሚያስችል ግልጽ የኃላፊነት ተዋረድ መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የልማት ግቦቹን አፈጻጸም ለማሻሻል የቀየሰቻቸውን ስትራቴጂዎች አስመልክቶ ለምክትል ዋና ፀሐፊዋ ገለጻ አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ለግቦቹ መሳካት ጠንካራ ትብብር እና ለትግበራው የሚያስፈልገውን የፋይናንስ መጠን ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።
የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ እያደረጉት ላለው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት እና አደረጃጀቶች የዘላቂ ልማት ግቦችን እንደ ሀገር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር አጣጥሞ ማስኬድ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ከተመድ ጋር ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በዓለም መድረክ የአፍሪካ ልማት ግቦች እንዲሳኩ የበኩሏን ሚና ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትሩ የገለጹት።
ኢትዮጵያ እና ተመድ የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ መስኮች ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ በውይይቱ ወቅት መገለጹን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026