አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፦የጥምቀትበዓልከኃይማኖታዊእሴቱባሻገርየከተማዋንመልካምገጽታበማስተዋወቅየኢኮኖሚተጠቃሚነታቸውንእያረጋገጠላቸውመሆኑንየባቱከተማነዋሪዎችገለጹ፡፡
በባቱ ከተማ ደምበል ኃይቅ ላይ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ለመታደም ወደ አካባቢው የሚመጡ እንግዶች መልካም ቆይታ እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ሁሉ ማዘጋጀታቸውን በማህበር የተደራጁ ወጣቶች ገልጸዋል፡፡
የጥምቀት በዓል ከኃይማኖታዊ እሴቶች ባሻገር በርካታ ማህበራዊና ባህላዊ ትውፊቶች የሚንጸባረቁበት ነው።
በባቱ የሚከበረው የጥምቀት በዓልም በርካታ ቱሪስቶች የሚሳተፉበት መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።
ባቱና አካባቢው የቱሪስት ኮሪደር መሆኑን ተከትሎ የአካባቢውን የተፈጥሮ፣ የባህልና የቱሪስት መስህብ የበለጠ በማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥርም ነው፡፡
በባቱ ከተማ ደምበል ኃይቅ ላይ በማህበር ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ወጣቶች በጥምቀት በዓል አከባቢያቸውን በማስተዋወቅ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኃይቁ በሞተር ጀልባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ወጣት ሳቃሳ በሪሶ በጥምቀት በዓል ለቱሪስቶች የጀልባ አገልግሎት በመስጠት አከባቢያቸውን እያስተዋወቁ ገቢም ለማግኘት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለእንግዶች የተሟላ የጀልባ አገልግሎት በመስጠት ላይ እነደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
በኃይቁ አካባቢ የዓሳ ምርቶችን በማቅረብ የሚተዳደሩት ወጣት ዙሪያሽ ግርማና አማኑኤል ወልደጊዮርጊስ፤ የጥምቀት በዓልን ለመታደም ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች መልካም ቆይታ እንዲኖራቸው እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኃይቁ ዳርቻዎች የዓሳ ምርቶችን ለቱሪዝቶች ለማቅረብ መዘጋጀታቸውንም ነው የጠቆሙት፡፡
ከምስራቅ ሀረርጌ በዓሉ ላይ ለመታደም የመጡት አቶ ሸዋንግዛው ንጉሴ በአካባቢው በተደረገላቸው መልካም አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።
በኃይቁ ዳርቻ አካባቢዎች ያለውን ውብ መልካዐ ምድር ለማልማት የተደረገው ጥረትም እጅግ የሚያስደስት ነው ብለዋል፡፡
በአካባቢው የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ይበልጥ በማስፋፋት በርካታ ጎብኚዎችን ወደ ለመሳብ መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ጫልቱ ቃበቶ በበኩላቸው ኃይቁን ለቱሪዝም ገቢ ለማዋል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025