
አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በፍጥነትና በጥራት እየተከናወነ መሆኑን የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደሳለኝ ጌታሁን ገለፁ።
የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 80 በመቶ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል።

የሞጆ ደረቅ ወደብን ወደ ሁለገብ የሎጅስቲክስ ማዕከል በመቀየር የወጪና ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ ከዓመታት በፊት የማስፋፊያ ግንባታ መጀመሩ ይታወቃል።
በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተወጣጡ ባለሙያዎች ፕሮጀክቱ ተመልክተዋል።
የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደሳለኝ ጌታሁን በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፥ የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ነው።
በ60 ሄክታር ላይ በሚከናወነው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የመሠረተ ልማት፣ የኮንክሪት ንጣፍ፣ የአይሲቲ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል፣ የአጥርና የመጋዘን ግንባታ ሥራዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ 80 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው፥ ፕሮጀክቱ በቀጣይ ዓመት ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።
የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የወደቡን የማስተናገድ አቅም፣ ቅልጥፍና እና ተዛማጅ የሎጂስቲክስ አገልግሎቶች ደረጃ ከመሰረቱ ይቀይራልም ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ሳይት ኢንጂነር ሊና ኑሩ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ መሰረታዊ የሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ የማጠናቀቂያ ስራዎች ለመስራት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ የኢትዮ-ጂቡቲን የንግድ ኮሪደር አቅም ታሳቢ በማድረግና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሸከም ታስቦ ነው እየተገነባ ያለው።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026