አዳማ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)የ፦ የስማርት አዳማ ፕሮጀክት የከተማዋ አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገለፀ።
ስማርት አዳማ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በአገልግሎትና የአሰራር ማሻሻያ ጭምር በጥናት ላይ የተደገፉ ተግባራት ፕሮጀክት ያቀፈ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በሪሶ ዶሪ ለኢዜአ እንዳሉት በከተማዋ ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል የስማርት አዳማ ፕሮጀክት እየተተገበሩ ነው።
ለፕሮጀክቱ ትግበራ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና አርተፊሻል እንቴለጀንስ ከፍተኛ ድጋፍና እገዛ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮጄክቱ የከተማዋ አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በፕሮጀክቱ በከተማዋ የሁሉም መስሪያ ቤቶች ሰነዶችን ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ መሆኑን ገልጸው፤ የመሰረተ ልማት፣ የትፊክ ፍሰት፣ የትራንስፖርት አገልግሎትና የጸጥታ ተቋማትን ለአብነት አንስተዋል።
ከ81 ሺህ በላይ የመሬት አሰተዳደርና አጠቃቀም ፋይሎች ወደ ዲጂታል በመቀየር ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ጨምሮ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
የኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ ለስማርት አዳማ ፕሮጀክት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው፤ የከተማዋ የኮሪደር ልማትና የኮደርስ ስልጠናም ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025