
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያ እና የመዝናኛ ስፍራ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በመዲናዋ በኮሪደር ልማት የተገነቡ መሰረተ ልማቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
ከእነዚህ የልማት ሥራዎች አንዱ የሆነው የአራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያ እና መዝናኛ ስፍራ ግንባታው ተጠናቅቆ ዛሬ በይፋ ወደ አገልግሎት ገብቷል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ከተማዋን ውብ፣ ጹዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

ዛሬ ለምረቃ የበቃው የአራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያና መዝናኛ ስፍራ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አካባቢው ከዚህ ቀደም ለተሽከርካሪ፣ ለእግረኞችና ለአካል ጉዳተኞች መተላለፊያነት አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሰው አሁን ችግሩን በሚቀርፍና ዘመናዊነቱን በጠበቀ መልኩ መገንባቱን ገልፀዋል።
አካል ጉዳተኞችም በቀላሉ መተላለፍ የሚችሉበት የአሳንስር መጓጓዣ መኖሩንም ነው የተናገሩት።
በውስጡ የሀገር ውስጥ አልባሳት፣ መዋቢያዎች፣ ወርቅና ብር መሸጫ ቤቶች፣ የስልክ መሸጫዎች፣ የፈጣን ምግብ አገልግሎት እና መሰል የንግድ አገልግሎቶች መጀመራቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠርና የገቢ ምንጭ መሆን መጀመሩን አንስተዋል።
የአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ በበኩላቸው፥ የመተላለፊያና የመዝናኛ ስፍራው በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ ብቁ አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መገንባቱን ተናግረዋል።
ስፍራው እግረኞች በቀላሉ የሚያልፉበት ብቻ ሳይሆን አረፍ ብለው የሚዝናኑበትና የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኮርፖሬሽኑ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን የማስተዳደር ኃላፊነት ያለበት ከመሆኑ አኳያ የአራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያና መዝናኛ ስፍራን ተረክቦ በማስተዳደር ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026