አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ዘላቂ ልማትንና የህዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የመዲናዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአስተዳደru የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
በዚሁ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፎች አመርቂ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
ከህዝቡ በተሰበሰበው ገቢ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው ዘላቂ ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ አርዓያ የሚሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹና ውብ የሆነች ከተማ ለማድረግ በመልሶ ግንባታ እና በመሠረተ ልማት ማስፋፋት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማን ዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ መቻሉም የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር ማድረጉን ገልጸው፤ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ባቀረቡት ሪፖርት፤ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ከእጅ ንክኪ ነጻ ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ 111 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቁመው ለ148 ሺህ 908 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
ግምገማው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በከተማዋ በተለያየ እርከን የሚገኙ አመራሮች እየተሳተፉ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025