የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Feb 7, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ጥር 29/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የክልሉ መንግስት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል።

በክልሉ በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማጠናከር ለጥራት፣ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብና ልማትን ለማፋጠን ትኩረት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

ገበያን ለማረጋጋት ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ በመሠረተ ልማትና በማህበራዊ ዘርፎች ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት በተለያዩ የልማት መስኮች የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የልማት ሥራዎችን የሚያደናቅፉ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማስቀጠል የህግ ተጠያቂነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት።

ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የችግኝ ተከላ ዝግጅት፣ የበልግ አዝመራ ሥራ፣የገጠርና የከተማ ኮሪደር ልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከሚሰራው ሥራ በተጨማሪ ነዳጅን ጨምሮ በተለያዩ ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመከላከል ይሰራል ብለዋል።

የሌማት ትሩፋትና የመስኖ ልማትን ጨምሮ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን የገበያ ማረጋጋቱ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኢንጂነር ነጋሽ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በየመስኩ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል አመራሩ በየአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ ወደልማት ለመቀየር ትኩረት ማድረግ እንዳለበት የገለጹት ደግሞ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።

ለዚህም ከተለመደው አሰራር አለፍ ብሎ ህብረተሰቡን በቅርበት በመደገፍ ተግቶ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

በተለይ በግብርና ዘርፍ የአርሶ አደሩን ሕይወት በተጨባጭ ለመቀየር በግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያለውን ተግዳሮት መፍታት ቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በከተሞች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማረምና የተለያዩ የልማት ኦኒሺየቲቮችን ማስፋት እንደሚገባም አንስተዋል።

የግምገማ መድረኩ ለቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025