አሶሳ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ከተረጅነት ለመውጣት የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
የክልሉ የአስፈጻሚ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቋል።
በግምገማው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ እና የበለጠ መስራትን የሚጠይቁ ናቸው ብለዋል።
በተለይ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረጉ መሆናቸውን አንስተው የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭን ማስፋፋት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የገቢ ምንጭ እና የኢኮኖሚ መሠረት መሆኑን አንስተው የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ከተረጅነት ለመውጣት የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የልማት ስራዎችን በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ በሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ ስራዎች በልዩ ትኩረት የሚከናወኑ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በክልሉ የመንገድ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታዎችን ለማከናወን የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
የትምህርት፣ የጤና እና የውሃ ፕሮጀክቶች የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የጥገና እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የመምህራንን አቅም ማሳደግ እንዲሁም የተማሪዎች ምገባ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።
በክልሉ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም እየተሻሻለ ቢሆንም አሁንም ገቢ በሚያስገኙ ስራዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዘንደሮ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 2 ቢሊዮን 250 ሚሊዮን ገቢ መሰብሰቡን ጠቅሰው ይህም ከእቅዱ 98 በመቶ የተሳካበት መሆኑን ገልጸዋል።
በአምስት ሚሊየን የኮደርስ ስልጠና በክልሉ እስከ አሁን አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረው ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ሌሎችም እንዲሰለጥኑ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025