አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፦የፈጠራ ሀሳቦች ኢትዮጵያ ለጀመረችው ዕውቀት መር የቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ፡፡
በሀገሪቱ የቢዝነስ ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሴቶች ብቻ የሚወዳደሩበት ፕሮግራም ይፋ ሆኗል።
የፈጠራ ውድድሩንየስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንተርፕርነር ሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት፣ እናት ባንክና በተባበሩት መንግስታት የሴቶች ጉዳይ በጋራ "ብሩህ እናት" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ነው።
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ በዚህ ወቅት፤ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸው፤ ከአጋር አካላት ጋር በመተባባር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ዛሬ ይፋ የተደረገውፕሮግራም ፈጠራ ሃሳብን ከማበረታታት ባለፈ ሴቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች መፍትሔ ማመንጫ መንገድ ነው ብለዋል፡፡
በዚህምየፈጠራ ሀሳቦች ኢትዮጵያ ለጀመረችው ዕውቀት መር የቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን አመላክተዋል።
ከሚመዘገቡ ሴቶች መካከል 50 ሴቶች በፈጠራ ሀሳባቸው ተለይተው ከመጋቢት 8 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ስልጠና ገብተው በፈጠራ ሀሳቦቻቸው ዙሪያ የሚሰለጥኑበት፣ የሚበቁበትና 10 አሸናፊዎች የሚለዩበት ይሆናል ብለዋል፡፡
ችግር ፈቺና ተጨባጭ የሆኑ ፈጠራ ሀሳቦች ወደ ተቋማዊነት የማሸጋገር እና ለአሸናፊዎቹ የብድርና መስሪያ ቦታም እንደሚመቻች ገልጸዋል፡፡
የኢንተርፕርነር ሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦሩ ሸና በበኩላቸው ኢንተርፕነር ሽፕ እንደ ሀገር ባህል ሆኖ እንዲጎለብትና ግለሰቦችም የራሳቸውን አቅም በመጠቀም ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ስራን በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ የቢዝነስ ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሴቶች የሚወዳደሩባቸው መስፈርትም በገበያ ተፈላጊነት እና ባለው አቅም በቀላሉ መሰራታቸው ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የእናት ባንክ ኦፕሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ትዕግስት አባተ በበኩላቸው፤ የሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የቢዝነስ ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሴቶች ብቻ የሚወዳደሩበት የሴቶችን ክህሎት የሚያዳብርና ችግራቸውን የሚፈታ ነው ብለዋል፡፡
ባንኩ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች በደረጃቸው ከ100 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር እንደሚሸልም ገልጸዋል፡፡
የቢዝነስ ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሴቶች ብቻ የሚወዳደሩበት ፕሮግራም ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 በሚከተለው ሊንክ መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
https://docs.google.com/forms/d/1vhHo lorWka27YYhisK1BIrnEQ27NOMomKeI7FCUB1Q/edit?edit_requested=true
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025