አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አካታች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት ስርዓትን በማፋጠን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።
ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ የግለሰቦችን ማንነት ለማረጋገጥና አገልግሎትን ለማሻሻል ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጿል።
በኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማንኛውንም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉበት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ "ፋይዳ" በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
አዋጁ ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ፣ ሌሎች መብቶቻቸውን የመጠቀም እድላቸውን ለማስፋት፤ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት እምነት እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና የተሳለጠ አሰራር መዘርጋትን ያለመ ነው፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል ይትባረክ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ በፍጥነት የገባችበት ነው፡፡
ከተቋማት ጋር ያለው ትስስር እና የማህበረሰቡ ግንዛቤ በየጊዜው እየዳበረ በመምጣቱ የተመዝጋቢዎች ቁጥር በፍጥነት እያደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ በአዋጅ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ እስካሁን 12 ሚሊዮን ያህል ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት ተመዝግበዋል ብለዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቤኔዘር ፈለቀ በበኩላቸው፣ ማንኛውም ለዲጂታል መታወቂያ የባዮሜትሪክ እና የዲሞግራፊ መረጃ በመስጠት የተመዘገበ ሰው መታወቂያውን የማግኘት መብት እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ማንኛውም ነዋሪ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚያከናውነው የተሳለጠ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚጠቅመው ተረድቶ በራሱ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ እንደሆነ በአዋጁ ተገልጿል ብለዋል፡፡
ነገር ግን ተቋማት ውስጣዊ አሰራራቸውን ለማዘመን ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያን አስገዳጅ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም ብሔራዊ ባንክ ከታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ(የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብን እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
ተቋማት የፋይዳ መታወቂያ መያዝን አስገዳጅ ሲያደርጉ ተገልጋዮች መጉላላት እንዳይገጥማቸው ብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም የተቀላጠፈ ምዝገባ የማድረግ ግዴታውን ይወጣል ብለዋል፡፡
ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አካታች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት ስርዓትን በማፋጠን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የፋይዳ ተመዝጋቢዎች የዲጂታል መታወቂያውን በዲጂታል ቅጂ፣ በወረቀት ወይም በካርድ በማሳተም መያዝ ይችላሉ ብለዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል ይትባረክ፥ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለ ክፍያ እንደሚፈጸም ጠቅሰዋል።
ነገር ግን ፋይዳን በካርድ አትሞ ለመስጠት ተቋማት እንደ ግለሰቦች ፍላጎት የተለያየ መጠን ያለው ክፍያ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል።
አንድ ሰው ለዲጂታል መታወቂያ የተጠየቀውን መረጃ አሟልቶ ከተመዘገበ በኋላ ከ30 ደቂቃ እስከ 7 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የፋይዳ ቁጥሩን የማግኘት መብት እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ግለሰቡ ሁለት ቦታ ላይ ከተመዘገበ መዘግየት ሊያጋጥም እንደሚችል ገልጸው፤ አሁን ላይ ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተናበበ አሰራርን የሚከተል በመሆኑ ችግሩ መፈታቱን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ አገልግሎቱን በሁሉም ክልሎች በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የምዝገባ ቁሳቁሶች በስርጭት ላይ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025