አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- የክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ሀገር በልጆቿ መልሳ የምትሰራበትን እድል የሚፈጥር ሂደት ነው ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የ‘ክህሎት ኢትዮጵያ’ ተሳታፊ ቴክኖሎጂስቶች የፈጠራ ሃሳባቸውን እና የሰሯቸውን ፕሮቶታይፖች አቅርበዋል፡፡
ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ሀገር በልጆቿ መልሳ የምትሰራበትን እድል የሚፈጥር ሂደት ነው ብለዋል፡፡
ለፕሮግራሙ ስኬታማነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ኢንስቲትዩቱ እና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የቅርብ ክትትል ያለው መሆኑን አንስተዋል።
የፕሮግራሙ ስኬት የጽናት ማሳያ ነው፤ ይህም የአመራር፣ የሙያተኛ፣ የተሳታፊዎችም ጽናት የታየበት ነው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡
የተጀመሩ የፈጠራ ስራዎች ከፕሮቶታይፕ አልፈው ምርት እስከሚጀመሩ ድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፉንና ክትትሉን እንደማያቆም መናገራቸውን ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው ሁለተኛው ዙር ፕሮግራም ከመጀመሪያው ይልቅ ብዙ ትምህርት የተወሰደበት እና ብዙ መሻሻሎች የታየበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም መካከል በጥብቅ የመረጣ ሂደት ውስጥ ማለፉን፣ የኢንደስትሪ ልምምድ በስፋት መካሄዱን፣ የተግባቦት ክህሎታቸውን የሚያሳድግ ስልጠና ማግኘታቸውን አንስተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ይህ ፕሮግራም ሀገር በቀል በሆነ እሳቤ በሀገር ልጅ ቴክኖሎጂስቶች ችግርን የመፍታት ሐሳብ የወለደው ፕሮግራም መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶች የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትኩረት በሆኑት ግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ኮንስትራክሸን፣ አይሲቲ፣ ሀይልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያሉብንን ችግሮች የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎቻቸውን አቅርበዋል ነው ያሉት፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025