ሀዋሳ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ):- በሲዳማ ክልል የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ የሚደረገው ክትትልና ዕገዛ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳድሩና ሌሎች የክልል አመራሮች በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተገነቡ ያሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በክልሉ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው።
ፕሮጀክቶቹ በወቅቱ እንዲጠናቀቁ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው አሁናዊ አፈጻጸማቸው በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሆነ አመልክተዋል።
የፌደራል መንግስት ባሳየው ቁርጠኝነትም የሀዌላ ቱላ-ውጅግራ-ያዬ-ወራንቻ የ85 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ግንባታ መጀመሩን ተናግረዋል ።
በአዲስ መልክ የተጀመረው የመንገዱ ግንባታ አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸው በቀጣይም ተገቢው ክትትልና እገዛ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የጉብኝቱ ዓላማም የመንገድ መሰረተ ልማቶች ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት እንዲጀምሩ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን አስታውቀዋል።
የክልሉ የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ በበኩላቸው በክልሉ በርካታ የአዳዲስ መንገዶችና ድልድዮች ግንባታና ጥገና ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም 149 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የአፈር ስራ የሚከናወንባቸውን 10 የመንገድ ፕሮጀክቶችን በዘንድሮ ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአስራ አንድ ድልድዮች ግንባታ አፈጻጻምም 70 ከመቶ መድረሱን ጠቅሰው በገጠር ተደራሽ መንገድ (URAP) ፕሮግራምም ከ136 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጻም የተሻለ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው "ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውም ጉልህ ነው" ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025