
ሰመራ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል በግማሽ በጀት ዓመቱ 15 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 62 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መውሰዳቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስታወቁ።
እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የአስፈፃሚውን የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፣ በግማሽ ዓመቱ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።
በክልሉ የሚገኙ ለም መሬቶች ወደ ልማት እንዲገቡ በማድረግ ከለማው የተለያዩ የሰብል ዓይነቶች ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በዚህም ከ20 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መሰራጨቱን ጠቅሰው፤ ምርጥ ዘር ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የተሻለ ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

የእንስሳት ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር ጤናቸውን መጠበቅ የሚያስችሉ ክትባቶች በስፋት መሰጠታቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ በግማሽ በጀት ዓመቱ 15 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 62 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መውሰዳቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ዘርፎቹም ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ግንባታና ቱሪዝም መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢንቨስትመንት እድሉ 7 ሺህ 609 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ፣ 3 ሺህ 619 ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ቋሚ የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።
በክልሉ በዳሊፋጊ ወረዳ፣ በሚሌና ሎጊያ ከተሞች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መጀመራቸውን አስታውሰዋል።
የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሟላት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን 23 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ውሃ ተደራሽ ለማድርግ ጥናት እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።
በክልሉ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ወረዳዎች መጨመራቸውን በሪፖርታቸው የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ 29 ወረዳዎች መድረሳቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ሰላም ከመቸውም ጊዜ በላይ ሰፍኗል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ትጥቅ ይዘው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርገው ወደ ሰላማዊ ህይወት መቀላቀላቸውን ገልፀዋል።
የሰላም ውይይቶችን በማዘጋጀትም የነበሩ ግጭቶች እንዲቀሩ ማድረግ የተቻለ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026