የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል - ኢትዮ ቴሌኮም

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፡- ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የተቋሙን የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም እንደ ሀገር ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም ትልቁን ድርሻ ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ለዕቅዱ ስኬታማነት ኢትዮ ቴሌኮም ለሶስት አመት የሚተገበር አምስት ግቦች ያሉት ስትራቴጂክ እቅድ ነድፎ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የአገልግሎት ጥራት፣ የገቢ ምንጭ ማስፋት፣ አዳዲስ የስራ እድል መፍጠር፣ ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማጠናከር የስትራቴጂክ እቅዱ አካል መሆናቸውን አብራርተዋል።

በተለይም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የሚያደርጉ የኔትወርክ ማስፋፊያዎችን መገንባትና የተቋማት አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ማድረግ የእቅዱ ዋና ግቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ማድረግና የዜጎችን መሰረታዊ እንቅስቃሴዎች የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን ማስረጽ የእቅዱ አካል መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ ስድስት ወራት 61 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን በመጥቀስ በቴሌ ብር አማካኝነት አንድ ትሪሊየን ብር ዝውውር መፈፀሙንም አክለዋል።

ወጪ ቆጣቢ የዲጂታል አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረግ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን አስታውቀው ምጣኔው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ43 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል።

ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 202 በሚሆኑ አካባቢዎች አዳዲስ የገመድ አልባ አገልግሎቶች ማስፋቱን አንስተዋል።

ስምንት ከተሞችን የ5ኛ ትውልድ ወይም 5ጂ ኔትወርክ እንዲሁም 67 ከተሞችን የ4ኛ ትውልድ ወይም 4ጂ ኔትወርክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎችን ዳግም ወደ አገልግሎት ለማስገባት በተሰራው ስራ 216 አካባቢዎች ሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በመግለጫቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025