ድሬደዋ ፤ የካቲት 8/2017(ኢዜአ)፡-መንግስት ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጥረት እያደረገ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ።
የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በ11 ከተሞች እየተተገበረ የሚገኘው "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" አካል የሆነው የድሬደዋ ፕሮጀክት የሁለተኛው ዙር የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ሰልጣኞች ምረቃ ዛሬ ተካሄዷል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደተናገሩት፤ መንግስት የሚስተዋለውን ስራ አጥነት በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
የስራ እድል ፈጠራውን ውጤታማ ለማድረግ በመደበኛነት ከሚከናወኑ ስራዎች በተጓዳኝ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በ11 ከተሞች በመተግበር ላይ የሚገኘው "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" የዚሁ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት አመታት በፕሮጀክቱ የታቀፉ 40 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች ከድርጅቶችና ፋብሪካዎች ጋር በማስተሳሰር የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መሰራቱን ጠቁመዋል።
የስራ ላይ ልምምድ ካደረጉት ውስጥም 34 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ለማድረግ በቆዩባቸው ፋብሪካዎችና ድርጅቶች የመቀጠር ዕድል ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
ፕሮጀክቱ የወጣቶችን የስራ እድል በማሰፋትና የስራ ባህልን እያሳደገ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዚህም በድሬደዋ ከሁለቱ ዙሮች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና የተሰተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በሶስተኛው ዙር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።
በምረቃት ስነ-ስርአቱ ላይ የተሳተፉት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው ወጣቶች በከተማዋ የልማት ስራዎች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬ የተካሄደው ምረቃም የዚሁ ጥረት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው የጀመሩትን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በፋብሪካዎችና ድርጅቶች የስራ ላይ ልምምድ ካደረጉ 972 የሁለተኛው ዙር የድሬደዋ የፕሮጀክት ተጠቃሚዎች መካከል 961ዱ የስራ ቅጥር ማግኘታቸውን የገለፁት ደግሞ የከተማዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ናቸው።
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በከተሞች የሚገኙ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 25 የሚሆኑ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የሚያደርጉበት ፕሮጀክት መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025