
አዳማ፤የካቲት 10/2017 (ኢዜአ).፦የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የመረጃ ትንተና ስርአትን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመላ ሀገሪቷ ለተውጣጡ የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች በአዳማ ስልጠና ሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍሰሐፅዮን፥ በኢኮኖሚ እድገትና ልማት ሂደት የዋጋ ግሽበት ቁጥጥርና ትንተና መረጃ አቅርቦትን ማሻሻል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚደረጉ ጥናቶች ለፖሊሲ ትልቅ ግብአት መሆናቸውን አንስተው፥ መረጃን በተሟላ መልኩ በጥራት መሰብሰብ እንደሚገባ እና የመረጃ ሰብሳቢዎች እውቀትና ክህሎት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የገቢ ግብርን ከመወሰንና ሌሎችም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራትን ለማከናወን አስፈላጊነቱን አብራርተው በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር)፤ የችርቻሮ የዋጋ ጥናት ለፖሊሲ ቀረፃና ውሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ለአገልግሎቱ በልዩ ትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም መረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ጥራት ያለው መረጃ ለመሰብሰብ በከፍተኛ ኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአዳማ ከዛሬ ጀምሮ ለ20 ቀናት በሚሰጠው ስልጠና ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተውጣጡ 200 መረጃ ሰብሳቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች እየተሳተፉ ነው።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026