ጅማ፣የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፡- የጅማ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግና አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የ"ሰማርት ሲቲ ፕሮጀክት" የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮ ቴሌኮምና በጅማ ከተማ አስተዳደር መካከል ነው።
በትናንትናው እለት በጅማ ከተማ አምስተኛው ትውልድን ሞባይል ኔትወርክ (5G) ያስተዋወቀው ኢትዮ- ቴሌኮም ዛሬ ደግሞ ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ መስማማቱን ገልጿል።
ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ ያሳልጣል፣ መረጃ አስተዳደርን ያቀላጥፋል፣ ደህንነትና ትራንስፖርትን ዘርፉን ለማሻሻልም ያግዛል ተብሏል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የጅማ ከተማን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ኩባንያው የሚጠበቅበትን ይወጣል ብለዋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም የተቀናጀ የቴሌኮምና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሰረተ ልማትን ለማቅረብ እንደሚሰራም አመልክተዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው ከተማዋን 'ስማርት ሲቲ' ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
ጅማ ከተማ የተሻለ መሰረተ ልማት ያላት፣ ሰላምና ደህንነቷ የተረጋገጠ ትሆን ዘንድ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀሟ ተገቢነት ያለው መሆኑንም እንሰተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025