አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ በዓለም የንግድ ምሕዳር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የኢትዮጵያ የንግድ ምልክቶችና ብራንዶች የሕግ ጥበቃ ማግኘት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ገለፀ፡፡
ባለስልጣኑ በዘርፉ ላይ ግልጽነት ለመፍጠር ያለመ የብራንድ አምባሳደሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄዷል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሉ ሞሲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ባለስልጣኑ አዕምሯዊ ንብረት ስርዓትን የመምራት እና ዘርፉ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወት የማድረግ ስራ እያከናወነ ነው።
የአዕምሯዊ ንብረት፣ የንግድ ምልክትና ብራንድ፣ የስነ ጥበብና ኪነ ጥበብ ውጤት ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የመመዝገብ፣ የማስተዋወቅ፣ ህጋዊ ጥበቃ እንዲያገኙ የማስቻል ስራ እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡
የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ጠንካራ ጥበቃ እንዲያገኙ የወጡ ሕጎች ተፈጻሚ በማድረግ አበረታች ስራዎች ቢከናወኑም ከሀገሪቷ ህዝብ ቁጥር፣ ከአገልግሎትና ምርት ብዛት አኳያ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ጨምሮ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ንግድ ምሕዳር ውስጥ እየገባች መሆኑን አስታውሰዋል።
በዚህም በዓለም የንግድ ምሕዳር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ንግድ ምልክቶችና ብራንዶች የሕግ ጥበቃ ማግኘት እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
በባለስልጣኑ የንግድ ምልክት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ትዕግስት ቦጋለ በበኩላቸው፤ የንግድ ምልክቶች ልዩ፣ የማህበረሰቡን እሴት የማይነኩና የፈጠራ ሀሳብ የታከለበት መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ 33 ሺህ ገዳማ የንግድ ምልክቶችመኖራቸውን ጠቅሰው፤ 18 ሺህ የሚሆኑት የሀገር እንደሆኑ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025