
ድሬዳዋ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በተደረጉ ድጋፎች ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ሀርቢ ቡህ ገለጹ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት የሚያግዝ ውይይት በዘርፉ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ዛሬ አካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የድሬዳዋ ምክትል ከንቲባ እና የአስተዳደሩ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ሀርቢ ቡህ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በአስተዳደሩ በማምረቻው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች በተደረጉ የተቀናጁ ድጋፎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።
የፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎትና መሠረተ ልማቶችን ተደራሽነት በማስፋት እንዲሁም የፋይናንስ ችግሮችን በማቃለል በተደረጉ ድጋፎች የኢንዱስትሪው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስችሏል።

በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተደረጉና የቀጠሉ ድጋፎች 32 የተዘጉና በግንባታ ላይ የነበሩ ፋብሪካዎችን ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ አስችሏል ብለዋል።
እነዚህን የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል የዘርፉ ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለሃብቶችና የፋብሪካዎች ተወካዮች በበኩላቸው አስተዳደሩ የማምረቻው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እያደረገ የሚገኘው ድጋፍና ቅንጅታዊ አሰራር የሚበረታታ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
የሮያል ፎም ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶሌራ ዳንጌ እንዳሉት ቢሮው ከየድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመሆን ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያደርጉት ሙያዊ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር የምርት ጥራት እንዲጨመርና ምርታማነት እንዲያደግ እያስቻለ ነው።
በቀጣይም የገቢዎችና የመሬት ልማት አስተዳደር ተቋማት ለዘርፉ ልዩና ፈጣን አገልግሎት የሚሰጡበት ማዕከላት ሊያመቻቹ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እየተደረጉ የሚገኙ ድጋፎች ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ተልዕኮና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳካት እያገዘ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የሽንቡሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ሀሪፍ አህመድ(ዶ/ር) ናቸው።
በተለይም በመናበብና በመደጋገፍ መሥራቱን አጠናክሮ መቀጠልና አልፎ አልፎ ለሚቆራረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መፍትሄ መስጠት የተሻለ ውጤት ያመጣል ብለዋል።
በድሬዳዋ ከተማ ከ24 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠሩ 364 ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በማምረት ላይ መሆናቸው በወቅቱ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026