ካራ-ቆርጮ የካቲት 11/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገሪቱ ከ230 በላይ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ከፀሐይ ሀይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር በመተባበር በደቡበ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ''ካራ-ቆርጮ'' እና ''ካራ-ዱስ'' ቀበሌዎች 425 ኪሎ ዋት የሚያመነጩ የሶላር ፕሮጀክቶችን አስመርቋል።
የአገልግሎቱ ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ክንፈ ነጋሽ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ተቋሙ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ ነው፡፡
በተለይ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀት ላይ የሚገኙ ከ230 በላይ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ከፀሐይ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ የሀይል አቅርቦትም ከ240 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን አቶ ክንፈ አመልክተዋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን ''ካራ-ቆርጮ'' እና ''ካራ-ዱስ'' ቀበሌዎች የተመረቁት የሶላር ፕሮጀክቶች የእዚሁ አካል መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ 425 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ከ6 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) በበኩላቸው የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የህብረተሰቡን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሃገሪቱ በየዘርፉ እያደገ የመጣውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተከትሎ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት መጨመሩን ጠቁመዋል
በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ 185 በላይ ቀበሌዎች አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደማያገኙ የገለጹት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ናቸው፡፡
የሀይል እቅርቦት እጥረት ፈተና ሆኖ መቆየቱን ያስታወሱት አስተዳዳሪው፣ በሐመር ወረዳ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር በርቀት ላይ ለሚገኙ ቀበሌዎች ከፀሐይ የኃይል አማራጭ እንዲያገኙ የተጀመረው ሥራ ስራ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።
ለኢዜአ አስተያየታቸውን ከሰጡ የአካባቢው አርብቶ አደሮች በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሀይል ባለመኖሩ በጨለማ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ገልጸዋል።
"አሁን ከጨለማ ወደ ብርሃን ተሸጋግረናል" ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025