አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶችን ሰርቶ የመለወጥ ዕድል ያሰፋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የ2ኛ ዙር ተጠቃሚዎች ምረቃ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።
መርሃግብሩ ከተለያዩ ስልጠናዎች ባሻገር ወጣቶች በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ለስድስት ወራት የተግባር ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ለስራ የሚያስፈልጋቸውን ክህሎትና ልምድ እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው።
በዛሬው ዕለትም በሁለተኛ ዙር ከ48 ወረዳዎች የተውጣጡ 13 ሺህ 527 ወጣቶች ተመርቀዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ በከተማዋ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት ከ142 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።
በኮሪደር ልማት መርሐ ግብሩም ከ70ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸው፤ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶችን ሰርቶ የመለወጥ ዕድል እያሰፋ መሆኑንም ገልጸዋል።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ አዲስ አበባን ጨምሮ በ11 የሀገሪቱ ከተሞች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጀመሪያው ዙር ከ15 ሺህ 731 በላይ ወጣቶች ስልጠና ማግኘታቸውን ገልጸው ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በሁለተኛው ዙር ከ24 ሺህ 213 በላይ ወጣቶች የዕድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንና ከ21 ሺህ በላይ የሚሆኑት የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን እንዲሁም ሶስተኛ ዙር እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
ተመራቂዎች የህይወታቸው የመጀመሪያው ምዕራፍ መስፈንጠሪያ ሊያደረጉት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር መሪየም ሳሊም በበኩላቸው፥ የዓለም ባንክ የወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ መሣተፉን ይቀጥላል ብለዋል።
ተመራቂ ወጣቶቹ የሀገሪቱን ዕድገት ከማፋጠን አንጻር ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ጠቅሰው፥ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደረግ አረጋግጠዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ፥ ቢሮው የስራ አጥ ምጣኔን ለመቀነስ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድን ተግባራዊ በማድረግ በርካቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ፕሮግራሙ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፥ ወጣቶቹ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በሁለተኛው ዙር ከ13 ሺህ በላይ ወጣቶች የልምምድ ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ 99 በመቶ የሚሆኑት በአለማማጅ ድርጅቶች ውስጥ የስራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በሁለቱም ዙሮች ከ20 ሺህ በላይ የከተማዋን ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው፥ አሁን ላይ በርካታ ወጣቶች የሙያም የስራም ባለቤት መሆን መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የ2ኛ ዙር ተመራቂዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከስልጠናው ለህይወታቸው የሚበጃቸውን ሙያዊ ክህሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራቂ ትዕግስት ነጋሽ እንዳለችው በከበሩ ማዕድናት ቆረጣ ዘርፍ ክህሎት ማግኘቷን ገልጻ ለልምምድ በተላከችበት ተቋም የስራ ዕድል ምግኘቷንም ተናግራለች፡፡
ተማራቂ ዘላለም ዘሪሁን በበኩሉ በብረታብረት ስራ ክህሎት ማግኘቱን በመናገር በቀጣይ የራሱን ድርጅት ከፍቶ ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025