አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡- ተቋማት የምርትና አገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ገለጸ፡፡
ድርጅቱ "በልህቀት ሞዴል አማካኝነት የጥራት ባሕልን ማሳደግ" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛውን ዙር የልህቀት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር)፣ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ መብራት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ድርጅቱ በ2000 ዓ.ም ሲመሰረት ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት ስርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን አለም አቀፍ የተወዳዳሪነት ብቃት ማሳደግ እና የጥራት ጽንሰ ሐሳብን በማስረጽ ጥራት የሀገሪቱ ባህል እንዲሆን ማገዝን ዓላማ በማድረግ ነው።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንትና የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ፤ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) መድረኩ ድርጅቶች በጥራት የተሻለ አፈጻጸም ካሳዩ ድርጅቶች ልምድና ተሞክሮን የሚወስዱበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ በተለይም ተቋማት ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራር በመከተል ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ለሀገር አድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ተቋማትም ምርትና አገልግሎታቸውን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ከሀገር ባለፈ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ ተቋማት ሃላፊዎች በበኩላቸው ፤ውይይቱ በቀጣይ ለተሻለ ምርትና አገልግሎት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በተለይም አሰራራቸውን ይበልጥ በማዘመን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ መብራት በበኩላቸው፤ ውይይቱ ከልምድ ልውውጥ በተጨማሪ የዘርፉ ምሁራን ስለጥራትና ልህቀት የጥናት ግኝቶቻቸውን ያቀረቡበት፣ ድርጅቶች የእርስ በእርስ ግንኙነት የፈጥሩበት፣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025