
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍስሃ ይትገሱ(ዶ/ር) አስታወቁ።
ለአካባቢጥበቃና ለጥራት በመጠንቀቅ የሚከናወን ምርት በዓለም ገበያ ተፈላጊ ነው ሲሉ የእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በሐዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ተገናኝተው በመከሩበት ወቅት እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10ሩ ወደ ልዮ የኢኮኖሚ ዞን አደጉ
በእያንዳንዱ ዞን ውስጥ ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ የፋብሪካ ፍሳሾችን የሚያጣሩ የፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያዎች (Zero Liquid Discharge) ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ በበኩላቸው በእስያ የሰራተኞች ደሞዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ አምራቾች የአፍሪካ ገበያን እዲያማትሩ እያስገደደ መሆኑን ገልጸዌል።
ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ አልባሳት እና ጨርቃጨርቅ አምራቾች መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው ሀገራቸው የእንግሊዝ ገዢዎችን ከኢትዮጵያ አምራቾች ጋር ለማስተሳሰር ጥረት እያደረገች መሆኗን መግለጻቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑን የስራ አንቅስቃሴ ተዘዋወረው በመመልከትም በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማጠናከር በእንግሊዝ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላትን ከእንግሊዝ ባለሀብቶቸ ጋር በማስተሳሰር ሊሰራ የሚችልበትን አጋጣሚ ማየት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ጠቁመው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር መግለጻቸው ይታወሳል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026