የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮ-እንግሊዝ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር

Feb 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና እንግሊዝ ዘመን ተሻጋሪ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአገሪቷ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ አንጄላ ሬይነር በእንግሊዝ መንግስት የውጭ የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO) የተገዙ 12 አንቡላንሶችን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስረክበዋል።

በልማት ቢሮው የተበረከቱ አንቡላንሶችን ቁልፍም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር እጅ ተረክበዋል።

እነዚህ አዳዲስ አንቡላንሶችም ለእናቶችና ህፃናት ፈጣንና የተሻለ የጤና ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውና የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ የታጠቁ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚሁ ጊዜ የእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር፤ በኢትዮጵያና እንግሊዝ መካከል በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ትብብራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸውም አገሪቷ የሚያጋጥሟትን ጫናዎች በመቋቋም ዕድገቷን ማስቀጠል የምትችል መሆኗን እንደተገነዘቡ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል ካሉ ግዙፍ የሁለትዮሽ ፕሮጀክቶች መካከል የሰብዓዊ ድጋፍና ትብብር ፕሮጀክት ትልቁ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በኢትዮ-እንግሊዝ የጋራ የብልጽግና ርዕይና ፍላጎት ላይ ገንቢ ምክክር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር በማስቀጠል ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስራ ሁለት አንቡላንሶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ፤ የእንግሊዝ መንግስት ለጤና አገልግሎት የሚውሉ አንቡላንሶችን በማበርከቱ ምስጋና አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍም ቅጽበታዊ አደጋዎችን ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ማሰልጠኛ ማዕከል በተደረገው የርክክብ ሥነ-ስርዓት የማኅበሩ የስራ ኃላፊዎች እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አላስቴር ማክፌል ተገኝተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር የተመራው ልዑክም በማኅበሩ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በቀጣይ የትብብር መስኮች ከማኅበሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025