ድሬዳዋ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፦ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ተወዳዳሪ መሆን የሚቻላው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማከናወን እና መተግበር እንደሚጠይቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ገለጹ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 10ኛው ዓመታዊ የምርምር ጉባዔ "በፈጠራ የተደገፈ የምርምር ውጤት ለዘላቂ ዕድገት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።
ለሁለት ቀናት በተሰናዳው የምርምር ጉባዔ ላይ በተለያዩ ዘርፎች የተደረጉ ምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዑባህ አደም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለአገርንና ለህዝብ የሚበጁ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል።
ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች ነባራዊ ዓለም ያገናዘቡና ችግር ፈቺ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው፤ ጉባዔው ይህን ለማጠናከርና አገራዊ ትልሞችን ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ታፈሰ አስራት (ዶ/ር) በበኩላቸው በተለዋዋጭ ዓለም ላይ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻለው ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች በጥራት ማከናወንና መተግበር ሲቻል ነው ብለዋል።
የጥናትና ምርምር ውጤቶችን በተቀናጀ መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል ለዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና መሠረታዊ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በየዘርፉ የሚካሄዱ ምርምሮች የአገርን ዘላቂ ጥቅሞች እና ከፍታ በሚያረጋግጡ መንገድ በተቀናጀ መንገድ እንዲተገበሩ ማድረግ እንደሚገባ ደግሞ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ነጋ አስራት (ፕሮፌሰር) ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ክስተቶችን እያስተናገገድ በመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን የዋጀና በፈጠራ የተደገፈ ጥናትና ምርምር በስፋትና በጥራት ማከናወን እንደሚሻ ገልጸዋል።
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ተማም አወል (ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ የሚካሄዱ ጉባዔዎች ችግር ፈቺ ምርምሮችን ወደ ተግባር ለመለወጥና ተሞክሮ ለመለዋወጥ ጥሩ መደላደል መፍጠሩን ተናግረዋል።
በጉባዔው ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በየዘርፉ የተከናወኑ 20 የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለውይይት እየቀረቡ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025