ጎንደር፤ የካቲት 13/2017 (ኢዜአ) ፡- የጎንደር ነዋሪዎች ለከተማዋ የኮሪደር ልማት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የጎንደር ከተማ የግማሽ በጀት ዓመቱ የኮሪደር የልማት ስራዎችን የሚገመግም የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሂደዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቱ የከተማውን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን አነቃቅቷል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለኮሪደር ልማቱ በራሳቸው ተነሳሽነት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማበርከታቸውን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የጉልበትና የሙያ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል።
ኮሪደር ልማቱ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ በዕውቀት ሽግግር፣ በተቀናጀ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በስራ ባህልን አበረታች ውጤት የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አለማየሁ አየለ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የጎንደር ኮሪደር ልማት አፈጻጸም ሌሎች ከተሞች ጭምር መልካም ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።
የአዘዞ ጎንደር የኮንክሪት አስፋልት መንገድን ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት በመንከባከብና በመጠበቅ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸጋዬ ሞሼ ፤ የኮሪደር ልማቱ ጎንደር ታሪኳን በሚመጥን ልክ እንድትለማ እድል የፈጠረና ለትውልድ የሚሻገር አኩሪ የልማት ስራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በከተማው ባለፋት ስድስት ወራት ታቅደው የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች አበረታች እንደሆኑ መገንዘባቸው የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙዐዝ በድሩ(ዶ/ር) ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025