
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ መሙያ ጣቢያ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደገለጹት በመዲናዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ሃይል መሙላት የሚያችሉ ጣቢያዎችን የማስፋፋት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ከተማ አስተዳደሩ ያስገነባው ይህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአንድ ጊዜ 16 ተሽከርካሪዎችን ሃይል መሙላት እንደሚያስችል ገልፀው እንደመኪኖቹ አይነት ሙሉ ቻርጅ ለማድረግ ከ20 እስከ 45 ደቂቃ እንደሚወስድም ጠቁመዋል።
የከባቢ አየር ብክለትን ለመከላከል እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም ጠቅሰዋል።
ታዳሽ ሀይልን ከማስፋትና የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስ አንፃር አስተዋፅኦ ያላቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ጣቢያው በውስጡ 1ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል ሲኒማቲክ ስክሪን የተገጠመለት አንፊ ቲያትር፣ 2 የህዝብ መዝናኛ ካፍቴሪያዎች እና የህጻናት ማቆያ እንዳሉትም ገልጸዋል።
እንዲሁም 800 ኪሎ ዋት ያለው ዝግጁ ጄኔሬተር ያለው ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደገፈ የሴኪዩሪቲ ሲስተም እንደተገጠመለትም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026