አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው ከህንድ የኢንዱስትሪ ማህበር(Confederation of Indian Industry) ባለሀብቶች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ውይይቱ ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሚሰማሩበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በዘርፉ ለሚሰማሩ የውጭ ኢንቨስተሮች ምቹ የኢንዱስትሪ የህግ ማዕቀፍ ከማዘጋጀት ጀምሮ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች መመቻቸታቸውን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ህንድ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላቸው ትብብር መጠናከር ለኢንዱስትሪ እድገት እንዲሁም ለቴክኖሎጂና ለዕውቀት ሽግግር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።
ለሀገራቱ ዜጎች የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ከመፍጠር ባሻገር በዓለም አቀፉ ገበያ የጎላ ድርሻ እንዲኖራቸው አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው ያሉት።
ከህንድ የኢንዱስትሪ ማህበር የመጡት ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ለመረዳት እንደቻሉ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025