
ሮቤ፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ በባሌ ዞን ባለፉት ዓመታት ድህነትን ለመቀነስ በተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመልከታቸውን የዞኑ ነዋሪዎች ገለፁ።
በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ውይይት በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ተካሄዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ ባለፉት ዓመታት ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ድህነትን ለመቀነስ በተከናወኑ ስራዎች ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ተመልክተዋል።
ከተሳታፊዎች መካከል አቶ አህመድ በከር እና አቶ ሐምዛ አደም በተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ምርታማነትን ለማሳደግ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን አድንቀዋል።
አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት ይልቅ የውኃ አማራጮችን ተጠቅሞ በስንዴና ገበያ ተኮር ምርቶችን በማልማት ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት መደረጉን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ወይዘሮ ሐስና ማህሙድ በበኩላቸው የኑሮ ውድነት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የመንግስት ሰራተኛውን እየፈተነ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም መንግስት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በልዩ ትኩረት እያከናወነ ያለው ተግባር ማጠናከር እንደሚገባው አንስተዋል።
በተለይም ምርትን በመደበቅ ሰው ሰራሽ የምርት እጥረት የሚፈጥሩ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት እንዲቀረፉ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሐኪም አልይ፤ መንግስት አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በግብርና ግብዓት አቅርቦት ላይ አበክሮ መስራቱን ገልጸዋል።
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከፍጆታ እቃዎች ድጎማ ባሻገር አምራችና ሸማቹን በማስተሳሰር ገበያን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የዞኑ የልማት ስራዎች ህዝቡን ባሳተፈ አግባብ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አብራርተዋል።
የኦሮሚያ የመስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ፤ ከህዝቡ የተነሱት የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናሉ ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026