አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።
በሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ ናቸው።
በክልሉ በመንግስት እና በግል የኢንቨስትመንት ልማት ስራዎች ላይ የታየው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ ከተሞች የትንሳኤ ዘመን ነው ያሉት ሚኒስትሯ ከተሞቻችን አምራች፣ የፈጠራ ማዕከል እንዲሁም የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
በከተሞች የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተዛማጅ የከተማ ልማት ስራ ላይ የተጀመሩ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ምልከታ ባደረጉበት የወልቂጤ ከተማ የሌማት ትሩፋት፣ የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች፣ እያደገ የመጣውን የግብርና ልማት ስራን ወደ ኢንዳስትሪ ማሸጋገር የሚያስችሉ ተቋማትን መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የላቀ አበርክቶ ማድረግ የሚችሉበትን እድል ተፈጥሯል ሲሉም ገልጸዋል።
የግብርና ኢንቨስትመንቱ ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጠርበት፣ የኑሮ ውድነት የሚረጋጋበት፣ ኤክስፖርት አቅምን በማሳደግ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ዘርፍ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
በወልቂጤ ከተማ የተመሰረተው እልፉ ባልትና ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የጠንካራ እንስቶች አብነት መሆኑንም ሚኒስትሯ ማስረዳታቸውን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታለ።
በልማት ስራ ጉብኝት መርሐ ግብሩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውም ተጠቅሷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025