የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ባለፉት አመታት ተገንብተው ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች መጠናከር አለባቸው

Feb 24, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦በብልጽግና ፓርቲ አመራር ሰጪነት ባለፉት አመታት ተገንብተው ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው የቦንጋ ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ገለጹ።

በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በቦንጋ ከተማ ተካሄዷል።

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በፓርቲው መሪነት በተከናወኑ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረው በጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ መሰረት ተስፋዬ፣ ባለፉት አመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዳደረጓቸው ተናግረዋል።

በቀጣይም ተጀምረው የቆዩ የመንገድ፣ የትምህርትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ፈጥነው እንዲጠናቀቁ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ አሰገደች ሀይሌ፤ የብልፅግና ፓርቲ ሀገርን ወደ ጥሩ ጎዳና ያሻገረና ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የቦንጋ ከተማ መጠጥ ውሃ ግንባታ መፋጠን እንዳለበትና በአርብቶ አደር አካባቢ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች መፍታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ፤ ብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በርካታ የማንነት፣ የኢኮኖሚና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን እየመለሰ መሆኑን አንስተው አሁንም ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በክልልና በፌዴራል መንግስት የሚፈቱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ተናግረዋል።

ሕዝቡም በየአካባቢው ያለውን እምቅ ሀብት ተጠቅሞ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ፓርቲው በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አቶ አወሉ አሳስበዋል።

ብልፅግና ፓርቲ በበርካታ ጫናዎች ውስጥ አልፎ ድሎችን ማስመዝገቡን የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጋትሎዋክ ሮን(ዶ/ር) ናቸው።

በእነዚህ ድሎች ውስጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበረ ገልፀው በቀጣይም ህዝቡ በየአካባቢው ትብብርና ድጋፉን ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከራሱ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ፀጋ ያለው በመሆኑ ይህን ተጠቅሞ ለመበልፀግ አብሮነትና አንድነትን ይጠናከራል ያሉት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።

ፓርቲው የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና በክልሉ የተጀመሩና ያልተጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025