ሐረር፤ የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል የህዝብን የልማት ጥያቄ ለሚመልሱ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
የሐረሪ ክልል የስድስት ወራት የፓርቲና የመንግስት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።
በተለይ ገቢን በመሰብሰብ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እና በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ይበልጥ ውጤት መመዝገቡን ነው የገለጹት።
የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን በማስፋት፣ ገበያን በማረጋጋትና ህገ ወጥነትን በመከላከል ልማቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩም አስታውሰዋል።
በኢንዱስትሪና በማኑፋክቸሪንግ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት በኩል ተጨማሪ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል።
ሰው ተኮር በሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራትም በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን ተናግረዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና አስፈፃሚ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025